“ፍንገጣ………3”

***

አፈንግጥ………….

 

እርግጥ ነው……

You can’t teach an old dog a new trick

ያረጀ ውሻን አዲስ ብልሃት ማስተማር አትችልም።

 

ግን ደግሞ……….

Don’t cut of your nose to spite your face

ፊትህን ለማናደድ ብለህ አፍንጫህን አታድማ።

 

ብዙዎችን ለማስተካከል ብለህ ከቀሩት ጋር

መገተትና መጋተት የራስን መጣል ቢሆንም።

ገፍቶ መሄድም መመለስ ነው።

 

በይትባህል ግትር ሆነው በፈጣን መንገድ

የዛጉትን ገፍትረህ በራስህ መንገድ

መጓዝ ባትችል እንኳን…….

 

ፊትህን ለማናደድ አፍንጫህን እንደማታደማው

አታስወግዳቸው።

ማስወገድ ማጣት ነው።

ይህ ማለት ለዝንብ ጭራ አትግዛ ማለት ነው።

ቆሻሻህን ማን ያነሳልሃል።

 

ማሳያ……

ጓደኛዬ ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባት ነው።

3 ውሽሞችም አሉት።

ቁጥሩ ለማነፃፀሪያ እንዲያመች እንጅ

እንደ ጠቢቡ ሰለሞን ብዙ ቅምጦች አሉት።

ለደግ ስራ ግን ቅምጥ ፕላን የለውም።

ሽፍደት ዘእምነገደ ይሁዳ ከሚሉት

ወገኖች መጣ ባይባልም እሱን እያወቀ

አለማውገዝ ግን አታመንዝር የምትለዋን ቃል

ለመዝለል ጠቅሞታል።ተጠቅሞበታልም።

(መጀንፐፕ)

ደብል ፌስ ጃኬት መልበስ ለታጣፊዎችና

ለተለጥፎ አስመችዎች እንደ ኒክ ኔም

በተሰጠበት ዘመን የነሱ አካል ሆኖ ተፈርጇል።

እናማ ልጁ ሆዬ……..

በእለተ አርብ ቅምጦቹን እቢሮው እየጠራ

በወረፋ ከቀመጨለ በኃላ…………..

(ሚስቱ ደውላ እንዳታስፎግረውና እንዳትነጅሰው

እንዲሁም እንዳታርፍበት  ፍላይት ሞድ ላይ አርጎ

ሲኮሽም ዋለና ምሳ ሰዓት ደረሰ)

ደውሎ ጠራኝና እንዲህም አለኝ።

ተራ በተራ እንዴት እንዳጫወታቸው ካወጋኝ

በኃላ ምሳ ሊሊጋብዘኝ ወደ ጠለፋ ቤት

እየጎተተ አስመረሸኝ።

በመሃል ሚስቱ ደወለች።

እ ምን ፈለግሽ አላት።

አይ ሰልክህ ሲዘጋብኝ ግዜ ሰግቼ ነው።

“ደህና ነኝ” ቻው ብሎ ዘጋባት።

የሰለሞን ዘር አይደል ችኮቹን እንዴት

በፈገግታ እንደሸኛቸው በክብር ተጠልቆ

በውርደት ጋርቬጅ ላይ የተወረወረው

ኮንዶም  ምስክር ነው።ምግብ ቤት ዱቅ አልን።

ዌይተሩ ገጭ አለ።

አስቡ ቀኑ አርብ ነው።እኔ ግን ጥብስ አዘዝኩ

ጮኸብኝ።

 

ምናባክ ፆም እኮ ነው። የዌይተሩን እጅ ጥብቅ

አርጎ =- ስማ የኔ በያይነት ይሁን እንዳይነካካ

እሽ አለው።

እኔም በጆሮው እንዲህ አልኩት።

ስጋቸው ፈስኮ በስጋ የሚፆሙ ብፁአን

ናቸው የሚል ቃል ወረደ እንዴ አልኩና

በልቤ….

 

ስጋህ ተነካክቶ ስጋ እንዳይነካካ ትላለህ

ያሳዝናል። አልኩት

በሽሙጤ ኩም ክው ይላል ስል

በምትኩ

እሽ እባክህ ዱቅ እኮ በቃ ፓትርያርክ

አላገጠብኝ።

በዚህ ማሳያ ዝም አይነቅዝም የሚለው

አባባል የዲያቢሎስ መሆኑን አስመስከሬያለሁ።

 

ማፈንገጤ በህይወት ላይ ፈር እንዳይስት

ስለረዳው የተወሰነ ብፁዓዊ ክሬዲት

ቢሰጠኝ አይከፋም።

ማስገንዘብና መጎሸም እንጅ

እሱን መቃወም ያላስቻለኝ ምክንያት ግን

You can’ teach an old dog a new trick

የሚለው ጥቅስ ሳይሆን አስተዳደግና ግንዛቤውን

ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።

 

የፍንገጣ ምልዓተ-ሃሳብ አሳይ እንጅ

አውጋዥ አይደለም።ለተቃርኖ ለመፈረጅ  ከተጠቀምክበት የሶቅራጥስ አጣ ይገጥምሃል።

ለማስገንዘብ ለማስታወስ ካዋልከው ግን

እንደ ማንዴላ በዳይህም ይከተልሃል።

ተጭኖህ የኖረን ትጫነው ዘንድ ይቻልሃል።

ይህ ይሆን ዘንዳ ግን

Don’t cut of your nose to spite

Your face

ይህ ማለት. ……………….

ተሳሳቹ እንዲታረም ብለህ አንተ አትሳሳት

አንተ አታሳስት ማለቴ ነው።

ማህበራዊ ፍንገጣ ሊብራል መሆን አለበት

(ያራዳ ልጅ አቀዝቅዘው ጀለሴ እንደሚለው)

ለምሳሌ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ብዙሃኑን

ሲቀጥፍ በፋኖ ዜማ ከአውድ ከተትን እንጅ

የጦርነቱ ምክንያት ምንድን ነው ብለን

አልጠየቅንም ።

የሃገር ፍቅርን በሚሰብኩ የፖለቲካ ቋንቋዎች

እና ዜማዎች ዘራፍ ብለን

እየተነዳን ተማገድን

 

ሃገር ይድን ዘንድ ማፈንገጥ ያስፈልጋል።

 

ያለያ በደም በአጥንት በማንነት የተዋሃደ

ሁሉ ሆድና ጀርባ ይሆናል።

 

እርቅ ከጥፋት በኃላ እንዳይሆን

ስትል ከፍትፍቱ ፊቱ ከማለት ተቆጥበህ

ሳይቃጠል በቅጠል ብለህ ግን ትጋ

ያኔ ሃገር ከነስታሊን እርስትነት ወደ

አብይ ጎዳና ትሾፋለች።

 

የፎረሼ አይዲወሎጅ ቀራምተው ሲያመጡ

ቅንጣቢውን ከሸመትህ ፋራነትህ

በዲግሪህና በለበስከው ብራንድ

አልባሳት አይደበቅም ።

ማወቅህን አብጠርጥሮ በመረዳትና

በማስረዳት እንዲሁም ተጋፍጦ ሃቅን

በማጥራት ግለጠው።

ወንፊት ማለት ከእንግዲህ ለአስተሳሰብ እንጅ

ለእህል ይሆን ዘንድ ህዋ የመድረሳችን ምስጢር

አይፈቅድምና በሃሳብ ከፍታ የመምጠቅ ሰብዕናን

መላበስ ግድ ይልሃል። ግድ

መቶ እጥፍ እየተመነደገ በሚሄደው

አለም ያንተ ተገትሮ መቆም ለራስህ

ኩሬ ለሌላው እንቅፋት ከመሆን በዘለለ

ፋይዳ የለውም።

 

ማህበራዊ ማፈንገጥ ማለት….

የለውጥ መንገደኞችን ማናጠብ

ሳይሆን የተልእኳቸው መዳረሻ ዉሉን

ሳይስት ግብ ብለው ለተፈፃሚነት

ተፍተፍ ለሚሉበት ያገር ሃቅ የራስን

አሻራ ማስቀመጥ ነው።

አሻራ ማለት የመኖር ትርጉም መገለጫ እንጅ

ለመኖር ሲሉ መላላጫ አይደለም።

እናም እንዲህ ብትል ያምርብሃል።

 

“ደው ኢልካ ንባሕሪ ብምዕዛብ ጥራይ

ባሕሪ ክስገር አይከአልን እዩ”

ትርጉም……

ባህርን ቆመህ በማየት ብቻ

መሻገር አትችልም።

ስለዚህ………

ያልመሰለህን ነገር በይምሰልና

በማስመሰል ተቀብለህ ስታስተጋባ

ጥበብህ በጥርጣሬ ውስጥ ይንሸራሸራል።

እንጅ ተቀባይነቱ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ

ማታ ነው።

የሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ህግ

መቻቻልን እንጅ መሻሻልን ስለማይወልድ

ላይ ላዩን ተዋደው ውስጥ ውስጡ መቃረን

የሞላቸው ሃሳቦች እያነደዱህ

ማሽላ እያረረ ይስቃል ለሚል ብሂል

አሳልፈው ይሰጡሃል።

የመንኮታኮት ብይኑም ማንም ሳይፈርድ

ብህ ይፈፀምብሃል።

አፈንግጥ ማለት ነባር ህጎችን ጥለህ

ተጓዝ ሳይሆን አርመህ ከዘኑ መንፈስ ጋር

ተራመድ ነው።

ስለዚህማ……….

 

“አል ኢልሙ ቀብለል ቀውሊ ወልዓመል”

ከንግግርም ከስራም እውቀት ይቀድማል

 

አሁንም አፈንግጥ

እስኪ ሆ በል ሲሉህ ሆ አትበል።

Leave a comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *